Tuesday, February 21, 2012

ትላንት ፒያሳ የሚገኘው በኒን መስጊድ በፌደራል ፖሊስ ተከቦ ዋለ


፪፩-፪-፳፩፪


ደረሰ ታሪኩ
ደ ብርሃን ሜድያ 
ከአዲስ አበባ-

ፒያሳ የሚገኘው በኒን መስጊድ



በአዲስ አበባ የአሊያ ትምህርት ቤት እና መስጂድ የተጀመረው የሙስልሞች የአደባባይ ተቃውሞ ስምንተኛ ሳምንቱን ባስቆጠረበት በዚህ ሳምንት ፒያሳ የሚገኘው በኒን መስጊድ በትላንትናው አለት (20 -2 - 2012 )በፌደራል ፖሊስ ተከቦ አንደዋለ ተዘገበ። 

በ እለቱ የበኒን መስጊድ ኢማም አና አሰጋጀ ወደ መስጊዱ የመጣውን አማኘ ለማሰገድ በሞከሩ ጊዜ ሀዝቡ በተቃወሞ ድመፅ  በማሰማት አንዳያሰግዱ ይከለክላቸዋል: የተቃውሞ ድምፁንም ያሰማል። ኢማሙም  ነገሩን በማራጋጋት  በደጋሚ ለማሰገድ ቢሞክሩም አማኙ ሕዝብ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። በሁዋላም  የመስጊዱ አመራሮች የፌደራል ፖሊስን ጠርተዋል። የፌደራል ፖሊስም ወደ መስጊዱ በምግባት አና አካባቢውን  በመውረር ስግደት እና ቀሪው ስነ ስርአት አንደካሄዱ አድርጉአል። የበኒን መስጊድ ኢማምም በፌደራል ፖሊሶች በመታጀብ  ስነ ስርአቱ ካበቃ በሁዋላ ከመስጂዱ ወተዋል። 
በሕዝብ የተመረጠው (17 አባላት ያሉት) ጊዜያዊ ኮሚቴ የካቲት 5 ቀን ከመንግሥት ጋራ ስላደረገው ውይይት ባቀረበው ሪፖርት መንግሥት እስከ የካቲት 26 ቀን ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት ቃል መግባቱን መገለፁ ይታወሳል ።

 


0 comments:

Related Posts Plugin for WordPress, Blogger...