By T, Staffer of De Birhan Media
01 November 2011
The famous Ethiopian predictor/prophesier of the future Sheikh Hussein Jibril lived in Ethiopia from 1811- 1908.
Most of his poems were predictions about the upcoming rulers of Ethiopia and socio-political situtaions of the country starting from the times of Zemene Mesfaent (Era of the Princes, of1769) to the present regime. For one who knows Ethiopian history well, the prophetic poems hit a 100% right. The poems are colloquial in writing and double-edged in meaning so they need to be read between the lines and with a deep knwolege of the Amharic language,Ethiopian history and religions. For eg, he terms Christianity as Amhara instead of calling it Christianity and similar kinds of usages.
Here I have selected few stanzas that I assumed relate to his prophesies of the present day Ethiopia and regime's fate.
ተፈሪ መኮንን የተያዘ እንደሆን
እንግዲህ ሐበሻ ምን ይበጀው ይሆን፣
(እህል ያልገዛ ሰው ምን ይበጀው ይሆን?)
አሥመራና ሸዋ ይሆናል እንዳይሆን
ወያኔ ተነሥቶ አሥመራ እሳት ሲሆን::
ጋ*ና ጉራጌ የሸዋ ሙንኪር
ሌት እንቅልፍ የላቸው ቀኑን በነገር፣
ሸዋን ይይዙታል አንድ እንኳን ሳይቀር
ድንጋዩን በድንጋይ አድርገው ንብርብር፣
አጃኢቡን ሳላይ መሬት ስትሆን ብር::
-----
በአሥመራ ወያኔ ከመጣ ችግር
መጀመሪያ አሥመራ ትሆናለች ቀብር
አክሱም ትጠፋለች በአንድ ቀን ጀንበር
ግሼን ላሊበላ ትሆናለች ቀብር
ሁሉም ይሸፍታል ሴት እናኳን ሳይቀር::
-----
ስንት እጃኢብ ያያል በዱኒያ የቆየ?
እኛ ባንደርስበት የልጅ ልጅ ጉድ አየ
ጥበብ እንዳይለምድ አሻቅቦ እያየ
የነጮችን ሥራ ብልግናን ገበየ
(አባቷም ዝም አለ ፈርጇን እያየ)::
----
ነገሩ እማይገባ የተወላገደ
በአሥመራ በትግሬ ሄዶ እየነደደ
እንዴት ያለ እሳት ከሸዋ ነደደ
ቢያጠፉት እምቢ አለ እየተዛመደ::
---
የአሥመራ ጦርነት ታኅሣሥ ሲጀምር
ብዙ ሰው ይጠፋል ነገሩ ሳያምር
አይሰድም መስሏቸው ሸዋ ብዙ ጦር
ወዲያው ሰደዳቸው በሰማይ በምድር
ወያኔው ይሞታል አያገኝም ነስር::
ሷሊህና ቃሲም አብደላህና ዙበኗር
በወልቃይት ብቅ አሉ ትግሬ ሲበረበር
ኩታበር ገራዶ ትሆናለች ጠጠር
ጎጃም ትጠፋለች ሳትውል ሳታድር
ብዙ ሰው ይጠፋል ያውም ከባላገር::
አሥመራ ተወግቶ ወልቃይት መርዙን ተፋ
ሽሬና መቀሌ ይሆናል የከፋ
እንቅልፍ እንዳይወስድህ እርብ ሳይጠፋ
ይመስላል ላየው ሰው ቂያማ የተደፋ
እርብ ስንቱን ጣለው ጠብቆ ወረፋ::
ጋይንት ንፋስ መውጫ ድራና ፎገራ
እርብ ላይ ሞልቶ ሲዘፍን ሲያጎራ
ነጋዴው ይጮሃል መቀሌና አሥመራ
ምን ይበጀው ይሆን ጅልጋና ፎገራ?
ሸዋ ደፈረሰ እህሊን ሳይዘራ::
---
መግዛቱን ይገዛል የዮሐንስ ዘር
ወዲያው ለጥቂት ቀን ይላል ፈንጨርጨር
ተፈሪን ጥላ አርጎ ሲያሳድድ ሲቀብር
ቢያዝ ደግ ነበር አገሩን ሳይቀብር
በቀር ሸዋ አይረጋም አትጠራጠር::
---
ይኸ ቻይና እሚሉት ዘራቸው ካልጠፋ
ችግር ይፈጠራል ይሆናል የከፋ
ማጥፋት ይሻል ነበር በአገር ሳይስፋፋ
ወልደን ሳንጥለው ልጃችን ሳይጠፋ
ጠብቀው ዘመኑን እስኪታይ በይፋ::
---
ምን መላ ይገኛል ጦር ቢያከማቹት
አልገዛም ካለ ከወንድም ከሴት
ሸዋ ካልመከረ ይሆናል ወንፊት
እባብ መርዙን ከተፋ ይመጣል ፍጅት
ይህን እየሰማህ እንዳትገባ እሳት::
በድርቡሽ ሲገርመኝ የመተማ እልቂት
የማይጨው ሲገርመን የአድዋ ጦርነት
መቀሌን አየሁት አረሁ በልቶት
ሸዋ በገዛ እጁ በጫረው እሳት
ስንቱ ሰው ይነዳል ውቅሮ አዲግራት::
---
አሥመራና ትግሬ ስትል ሰገደይ
እባብ ከተፍ ይላል ማምጫው ሳይታይ
ሸዋ የዚያን ጊዜ ይላል ዋይ! ዋይ!
ጀርባውን ምች መታው ወደ ትግሬ ሲያይ::
---
ዘመን ተለውጦ ጥቅምት ሲደርስ
በአሥመራ ከተማ ይነፍሳል ነፋስ
የዚያን ቀን ሐበሻ ይላል ፈረስረስ
ሃምሳ ቀን ይቆያል ሴት ወንዱ ሲያለቅስ
ወንፊት ጉድ እስኪወልድ እስኪሆን አራስ::




