Wednesday , 30 October 2013

Category Archives: አማርኛ ፅሑፎች

ለስኳር ፋብሪካ ግንባታ እየተባለ ከህዝብ ካዝና የሚወጣው በጀት በኢህአዴግ ባለስልጣናት እየተዘረፈ ነው: ትሕዴን

17 October 2013 በሃገሪቱ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀችት እየተባለ በየዓመቱ የሚመደበው በጀት ለሚፈለገው ስራ ሳይውል በስርዓቱ ባለስልጣንት ይዘረፋል፣ በሚኒስትር ማእረግ የስኳር ኮርፖሬሽንን ሲመራ የነበረ አባይ ጸሃየ ከ 150 ሚልዮን ብር በላይ መዝረፉን ከደረሰን ዘገባ መረዳት ይቻላል፣ አባይ ጸሃየ በሰራው ወንጀል ተከሶ ወደ ፍርድ መቅረብ ሲገባው መ/ቤትን በመቀየር ወደ ሌላ የስራ መመደቡ ያልተዋጠላቸው የኮርፐሬሽኑ ሰራተኞች ዝውውሩን በመቋወም በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ገልጸዋል፣ በወልቃይት ... Read More »

በሑመራ ከተማ ወጣቶችን በውትድርና ሞያ ለመመልመል በእህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች ሰፊ ቅስቀሳ የተካሄደ ነው፣

በደረሰን ዘገባ መሰረት በሑመራ ከተማ ከ 18-22 የእድሜ ክልል የሚገኙ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች ውትድርና  እንዲመለመሉ ቅስቀሳ እየተደረገ ሲሆን ፥ የስርዓቱ ካድሬዎች ውትድርናን የተመለመለ የትምህርት ደረጃው እየታየ በኮምፒዩተር ፤ በመካኒክና ሌሎች ሞያ እንዲሰለጥን ይደረጋል የሚል የማይተገበር ቃል እየገቡ ወጣቱን ለማታለል ቢሞክሩም ወጣቶቹና ቤተሰቦቻቸው ግን ቅስቀሳ ለማዘናጋት የሚደረግ የተለመደ ነገር መሆኑን በመገንዘብ ውድቅ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሏል፣ ከዚህ ቀደም ባቀረብነው የዜና ዘገባ ... Read More »

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት አቆሙ

መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከአስተዳደሩ ጋር የብቃት መመዘኛ ፈተና ዙሪያ መግባባት ባለመቻላቸው ትምህርት ማቆማቸው ተሰማ፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስተላለፈው ውሳኔ በተማሪዎቹና በዩኒቨርሲቲው መካከል አለመግባባትን በመፍጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩኒቨርሰቲውም የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ግቢ ለቀው መውጣታቸውን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብቃት ማረጋገጫ እንዲወስዱ ሲጠይቃቸው ተማሪዎቹ በቂ የዝግጅት ጊዜ ... Read More »

የትህዴን ደጋፊዎች ግንቦት-7 እያካሄደው ባለ ስብሰባ መገኘታቸውን የትህዴን የህዝብ ግንኝነት ገለጸ

ትህዴን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኘው ግንበት-7 ጋር ተባብሮ  ለመስራት መግባባት ላይ ከመድረሱም በላይ በተግባር በተለያየ መልኩ ሲተጋገዙ የቆዩ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ  የትህዴን አ ባላት የጉንበት-7 አ መራር ከአ ባላቱ ጋር በተለያዩ ሃገራት እያካሄደው ባለ ስብሰባ በመገኘት አንድነታችንን አ ጠናክረን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን ሲሉ ለግንበት-7 ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን  የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣ በስብሰባው የተገኙ የትህዴን ተወካዮች አ ያይዘው እኛ በዚሁ ስብሰባ ... Read More »

አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ28 ሩዋንዳዊያን ነጻ የትምህርት እድል ሰጠ

አርባምንጭ መስከረም 22/2006 የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው የትምህርት ዘመን ከኢትዮጵያዊያን መደበኛ ተማሪዎች ጋር ለሚማሩ 28 ሩዋንዳዊያን ዘጎች የትምህርት እድል መፍቀዱን አስታወቀ። በዩኒቨርሲቲው የኮርፖሬት ኮሙኒከሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገነነ ገደቡ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ለሩዋንዳዊያን የትምህርት እድል ሲፈቅድ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ ደረጃ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ብቻ በሚሰጠው በአየር ትንቢያ ትምህርት ክፍል እንዲማሩ የተፈቀደላቸውን ሰባት ... Read More »