11-6-2016
Dr. Negeri Lencho, the Dean of Addis Abeba University’s School of Journalism and Communication’s and Board Member of the Oromia Radio and Television Organization, was quoted by state media today saying the the school will start PhD in Journalism Program in the next academic year. The News could surprise many since there are at least seven Ethiopian universities currently offering undergraduate and postgraduate level degrees in Journalism and he majority are jobless, exiled or detained.
Every year hundreds if not thousands of Ethiopians graduate with journalism degrees but many find themselvess unemployed due to the absence of a media infrtasturcture and a market that meets the number of grdauates and the lack of press freedom in Ethiopia.
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚኒኬሽን ትምህርት ቤት ከሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ጀምሮ በመገናኛ ብዙኃንና ኮሚኒኬሽን ጥናት የዶክትሬት ዲግሪ መርሐ ግብር ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡
ዩኒቨርስቲው በሚከፍታቸው አዳዲስ የትምህርት መርሐ ግብሮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡
የትምህርት ቤቱ ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በዘርፉ ከፍተኛ አገራዊ ፍላጎት በመኖሩ በጥናትና ምርምር የእውቀት ደረጃውን ከፍ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ ከዚህ በተጨማሪ የሕዝብ ግንኙነትና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ትምህርትን በድህረ ምረቃ መርሐ ግብር መስጠት ይጀምራል፡፡
በቅድመ ምረቃ መርሀ ግብርም በሕዝብ ግንኙነትና ማስታወቂያ እንዲሁም በኮሚኒኬሽን ጥናት የትምህርት ክፍሎችን ይከፍታል፡፡
የትምህርት ክፍሎቹ በተቋማዊና ማህበራዊ ተግባቦት በጎ ተፅእኖ እንዲያሳርፉ የታለመ ሲሆን በመገናኛ ብዙኃን እንቅስቃሴ ላይም ለውጥ ለመፍጠር እንደሚያግዙ ተጠቅሷል፡፡
Source: EBC