በኢትዮጱያ ከሚከበሩ በኣላት ለየት ባለ ስነ ስርአት ከሚከበሩ በአላት ዉስጥ አንዱ ጥምቀት ነዉ።ጥምቀት ከሌሎች በአላት ለየት የሚያደርገዉ ህዝቡ በአሉን የሚያከብረዉ እንደ ሌሎች በአላት በየ ቤቱ ሳይሆን ታቦቱ በሚያድርበት ስፋራ በመሆኑ በእምነቱ ተከታይና ባልሆኑም ሰዎች በኢትዮጱያ ልዩና ተናፋቂ ያደርገዋል። በአሉ ከመንፈሳዊ ስነ ስርአቱ ባሸገር የተለያየ አድምታ ያለዉ ነዉ።
በጥቂቱ የበአሉን አከባበር በመንፈሳዊ በኩል እንመልከት . ከተራ . በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ታቦታት ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ወንዝ ወይም ለጊዜዉ በተሰራ ስፋራ ወርደው ለማረፊያ በተዘጋጀላቸው ቦታ ያድራሉ፡፡ወደ ስፍራዉም የየአጥቢያው ሕዝብም በነቂስ ወጥተው ታቦታቱን በማጀብ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በመሄድ ያገለግላሉ በዕለቱ እዚያው ያድራሉ፡፡ ካህናት ሌሊቱን በማኀሌት ስብሐተ እግዚአብሔር ሲያደርሱ ቆይተው የቅዳሴው ሥነ-ሥርዓት በመንፈቀ ሌሊት ተጀምሮ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ይፈጸማል፡፡ ጥምቀት ጥር 11 ቀን ጠዋት በባሕረ ጥምቀቱ ላይ ጸሎት ይደረግና ውኃው ይባረካል፡፡ ሕዝቡም በተባረከው ውኃ ይረጫል፡፡ከዚህ የሚቀጥለው ታቦታቱን የተሸከሙ ካህናት ከድንኳን ወጥተው ለዝማሬ ማኀሌት በተዘጋጀው አውደ ምሕረት ላይ ይቆማሉ፡፡ መዘምራኑ በዓሉን በተመለከተ ቃለ ማኀሌት በመቃኘት ያሸበሽባሉ፡፡ ከዚያ በወጣት መዘምራን ዝማሬ ጉዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሆናል፡፡ በዋዜማው እንደተደረገው ሕዝቡ ሁሉ በቋንቋው፣በባህሉ መሠረት እያሸበሸበ በእልልታና በሆታ በማጀብ ይጓዛል፡ እነዚህ ክንዋኔዎች የራሳቸዉ የሆነ ትርጉም በምሳሌ የተቀመጡ መሆናቸዉን ልብ ልንለዉ ይገባል። ከላይ የተጠቀሰዉ መንፈሳዊ ክንዋኔዎች ሲካሄዱ ጉን ለጉን የሚደረጉ የበአሉ ገፁታ የሆነ ስነ ስርአቶች አሉ።
በአአ በአሉ በድምቀት ከሚከበርባቸዉ ስፍራዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰዉ የጃንሜዳ የጥምቀት በአል። በጃንሜዳ የጥምቀት በአል መነሻዉ ስንመለከት 1933 አም ጀምሮ በአሉ በዚህ ሰፊ ቦታ እንዲከበር ተወስኖ እስኳሁንም እያስተናገደ ይገኛል።የተወሰነበትም ምክንያት ከገነተ ልኡል ቤተ መንግስት የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አቅራቢ የሚገኝዉ ሰፊ ቦታ ይሄ ስለሆነ ነበር። . . በወቅቱም ደማቅ እንዲሆን ያረገዉ ንጉሱም፣ ፓትሪያርኩም፣መሳፍንቱም ሆኑ የሀገሪቷ ታላላቅ ሰዎች በስፍራዉ ተገኝተዉ በማክበራቸዉ ነዉ ። በአሉን በማስታከክ ደግሞ የተለያዩ የብሄረሰብ ጭፈራዎች ፣ልዩልዩ አዝናኝ ጨዋታዎች ና የተለያዩ ነገሮች የሚሸጥበት ቦታ ነዉ።
ሌላዉ ከብሄረሰቡ ጨዋታ ጭፈራ ዉጪ ሊጠቀስ የሚችለዉ ጥምቀት በመጣ ቁጥር የሚጠበቀዉ የታዳጊዎችና የወጣቶች የሀርሞኒካ ጭፈራ ።ጭፈራዉ ሴትና ወንድ ሆነዉ የሚጨፍሩት ሲሆን ወንዱ ሴቷን ለጭፈራ ጋብዛ የሚያስደስትበተና ከተሳካለት ይዞት የሚሄድበት ጭፈራ ና ጨዋታ ነዉ።በብሄረሰቦቹም ጨዋታ እንደዚ አይነት ክስተቶች ሊኖሩ የሚችልበት እድል ሰፊ በመሆኑ ከመንፈሳዊ በአልነቱ ባሸገር ወጣቱ የሚገናኝበት ሰፊ በአል ነዉ ጥምቀት።ለዚህም አይደል ስነ ቃሉም እንዲ የሚለዉ “ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ።” በጥምቀት ጨዋታ ተገናኝተዉ ይዞ እስከ ጋብቻ የደረሱ ሰዎች እንዳሉ መመልከት የ ጨዋታዎችን አድምታ እዚ ድረስ መሆኑ መገንዘብ እንችላለን። ልዩ ልዩ ጨዋታዎችን ለመመልከት ያህል .አይን በጨርቅ ተሸፍኖ እንስራ መስበር የተለያየ አይነት የኳስ ጨዋታዎች በመዘፍዘፊያ ዉስጥ ሳህን ተቀምጦ ሳንቲም ማስቀመጥ እና ሌሎች መሰለል አስደሳች እና አዝናኝ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። እንደምሳሌ ጃንሜዳ አልን እንጂ በሌሎች በከተማዉ ቦታዎች በሚገኙ ሜዳዎች በድምቀት የሚከበር በአል ነዉ።
በተጓዳኝም በሀገሪቷ ከሚገኙ ከተሞች በጎንደር በድምቀት የሚገበር በአል ነዉ። በአሉ ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ ድረስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በክልሎ ባህሉና ትዉፊት መሰረት በድምቀት ከሚከበርበት ከተሞች አንዱ ጎንደር ነዉ። የጥምቀቱ ስነ ስርአት የሚካሄደዉ በፋሲለደስ ገንዳ ዉስጥ ሲሆን ይህን በአል ለመታደም ከተለያዩ አለም ክፍላት ጎብኝዎች በመምጣት ስነ ስርአቱን ይከታተላሉ።እናም ከተማ በነዚህ የበአል ቀናት በእንግዶችና በከተማዉ ኗሪ ደምቃ ትዉሏለች ። በጎንደር በአሉን ደማቅ እንዲሆን የሚያረገዉ ዋንኛዉ አርባ አራቱም ታቦታት መገኛ ስፋራ በመሆኑ ጭምር ነዉ። . በመጨረሻም ይሄ ኢትዮጱያዊ የሆነዉ በአላችን ከጊዜ ወደጊዜ እንዳይበረዝና የተለየ አድምታ እንዳይኖረዉ ሁሉም የበኩሉን ኣስተዋፆ በማድረግ ይበልጥ ደምቅ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ ነዉ።ሌላዉ ሊበረታታ የሚገባዉ ከቅርብ አመታት ጀምሮ በየ ሰፈሩ የሚገኝ ወጣቶች ታቦተ ህጉ በሚወጣበትና በሚገባበት ስፈራ የሚያደርጉት ስነ ስርአት ይበል የሚያሰኝ ነዉ በማለት በአሉን ለምታከብሩ በሙሉ መልካም በአል እንዲሆንላቹ በዚህ አጋጣሚ ተመኘን።
በዳግም ታምሩ
source: Addis Insight




