ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ
ጥቅምት 19፣ 2017 እ.አ.አ
የዛሬ ሦስት አመት ታህሳስ 10 ቀን 2007 ዓ›ም “ግፍና አፈና ዐመጽን ይወልዳሉ፤ የዐመጸኛ አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው (መ.ምሳሌ ም.22፣ ቁ.14)” በሚል አርዕስት ለንባብ ባበቃሁትና በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ በገመገምኩበት ጽሁፍ ይህን ከትቤ ነበር፤ “አንድ ሕዝብ በላዩ ላይገዢዎች እየተፈራረቁበት ረዘም ላለ ጊዜ በአገዛዝ ሥርዓት ሥር
ስር ሊቆይ ይችል:: ይሁንና እድሜልክ የገዛ አፋኛ ሥርዓት ግን የለም:: ሥርዓቱም እንደ ድርጅት፣
ሹማምንቱም እንደ ሰው የጉብዝናእድሜያቸው የተወሰነ ነው:: የአፈናን ስልት በመለዋወጥና
ሸምቀቆውን በማጥበቅም እድሜንማራዘም የሚቻል ቢመስልም በተቃራኒዉ ውድቀትንም ያፋጥናል::
ግፉ እየበረታና የመብትጥሰቱም መረን እየለቀቀ በሄደ ቁጥር የሕዝብ ትእግስት ይሟጠጣል::
ሕዝብ መቆጣት ከጀመረናቁጣውም ወደ አደባባይ አመጽ በተቀየረ ጊዜ የግፍ አገዛዝ ወደ መቃብር፣
ግፈኞቹም ወደ ዘብጥያእንደሚወርዱ እርቀን ሳንሄድ ባለፉት አምስትና አሥርት አመታት ውስጥ
በአለም የታዩ ሕዝባዊነውጦችንና ያስከተሉትን መዘዝ ማጤን በቂ ነው::” የዚህ ጽሁፍ አላማም
የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግ ቀን ይመጣል እያለ አምቆ የያዘው ብሶትና ክፌት ሊፈነዳ ጥቂት
ስለቀረው ሥርዓቱ በጊዜ እራሱን ያርቅ፤ ካልሆነ ግን የማይቀረው አመጽ ይነሳል። የሥርዓቱም
ፍጻሜ እንዳያምር ይሆናል። የሚል ማሳሰቢያ ጭምር ነበር። አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ
ነገሮች እያፈጠጡ መጡ። ይህን ጽሁፍ ምሉውን ለማንበብ ከዚህ ገጽ ሥር ያለውን
ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።[1]
ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አመታት በማያባራ የሕዝብ ተቃውሞ ስትናጥ ቆይታለች። ከአንድ አመት በፊትም መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም “ግፍ በገፍ የሞላባት አገር” በሚል በጻፍኩት አጭር ጽሑፍ ይህን ሃሳብ አቅርቤ ነበር፤ “ከአፋኝና ታፋኝ የፖለቲካ አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜልንላቀቅና
ጭቆናን ታሪክ አድርገን ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና ልንሸጋገር
የምንችለውግፉአን ብቻ ሳይሆኑ ግፍ ፈጻሚዎቹም አብረው ነጻ ሲወጡ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም አገርንየማዳን ትግሉ ለአገዛዝ ሥርዓቱ የመጨቆኛ መሳሪያ
በመሆን እያገለገሉ ያሉ አጋር ድርጅቶችን እናግለሰቦችን ከወያኔ ጉያ
ማውጣትና የሕዝብ ወገንተኛ እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ግቡ ማድረግአለበት፡፡ ለዚህም በመሳሪያ አቅም፣ በፖለቲካ አደረጃጀት፣ በገንዘብም አቅም
ይሁን ሰፊውንየአገሪቱን ክፍል በማስተዳደር ዕረገድ የማይናቅ ድርሻ
ያላቸውን ኦህዴድ፣ ብአዴን እና ሌሎችአጋር ድርጅቶችን የትግሉ አካል
እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ከወዲሁ ማመቻቸት ትግሉን ከማፋጠንባለፈም
ሊደርስ የሚችለውን የጥፋትና እልቂት አደጋም የመቀነስ ኃይል ይኖረዋል፡፡[2]”
የአገዛዝ ሥርዓቱ በጠመንጃ ብቻ ሊቆጣጠረው ያልቻለውን የሕዝብ ቁጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመደንገግና የፈላጭ ቆራጭነት ስልጣን የተሰጠው ኮማንድ ፖስት በማዋቀር ቁጣውን ለማፈን ያደረገውም ጥረት ከሽፏል። ለዚህም ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በተጠናከረ መልኩ የቀጠለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጥሩ ማሳያ ነው። ይህ የተቀጣጠለው ተቃውሞ እያደርም ሥርዓቱን ይቦረቡረው ጀምሯል። ትላንት ፊታቸውን ከልለው የተቃውሞ ምልክት በእጆቻቸው እያሳዩ ለሕዝባቸው ድጋፍ ይሰጡ የነበሩ የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች ዛሬ በይፋ ከሰልፈኛው ጋር ተቀላቅለው ድጋፋቸውን ሲሰጡ በግላጭ እያየን ነው። ከሥርዓቱ ምስረታ አንስተው በከፍተኛ አመራርነት ላይ ያገለገሉ ባለስልጣናትም፤ አባዱላ ገመዳ እና በረከት ስምዖንን ጨምሮ የጊዜውን መጨላለም አይተው ሳይዳፈን በፊት ገለል ማለታቸው ሌላው ሥርዓቱ ክፉኛ መታወኩን ማሳያ ምልክት ነው። ሌሎች በግልጽ ጎልተው የሚታዩ በርካታ ምልክቶችንም መጠቃቀስ ይቻላል።
Click Here:
ሲያልቅ አያምር፤ “የሥርዓቱን አሟሟት ያሳምርልን!”






