June 17, 2015

The Lideta Federal High Court of Ethiopia has finished the hearing of human and material evidences that have been presented to it by the Public Prosecutor since last week on 10 defendants under the file of Zelalem Workagegnehu, De Birhan’s co-blogger. Sheleme Bekele, the middle judge, said the Prosecutor’s request for additional time to present evidences against the defendants has been ruled out. Temam Ababulgo, the solicitor for seven of the defendants argued before the Court that all the evidences presented against his clients were found after they were detained and this was contra to the law particularly Article 146 of the Criminal Law and therefore all the evidences that the Prosecutor presented were not related to the charges. The Prosecutor, on its part, said that the solicitor has not presented tangible evidences and the evidences it presented were acceptable. The Prosecutor also asked the Court to reject the solicitor’s opposition and called for the Court to give verdict based on the already submitted evidences.
The Court then gave a new appointment to July 8, 2015 to give verdict on the Public Prosecutor’s evidences. Three local politicians under the same file: Abraha Desta, Daniel Shibeshi and Yeshiwas Assefa have been transferred to Kaliti prison from Kilinto, where they have been held together with the other seven since November 2014.
Source: Social Media sources (Eyoel Fisseha)
በእነዘላለም ወርቅአገኘሁ ክስ መዝገብ ስር የሚገኙት ተከሳሾች ለብይን ተቀጠሩ
በሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው የሚገኙትና ጉዳያቸው እየታየ የሚገኘው እነዘላለም ወርቅአገኘሁ ከረፋዱ 4፡30 ላይ ልደት በሚገኘው 19ኛ ወንጀል ችሎት ቀረቡ፡፡
ችሎቱ ዛሬ ተሰይሞ የነበረው በተከሳሾቹ ላይ አቃቤ ህግ ባቀረበው የሰነድና የሰው ማስረጃ ላይ ብይን ለመስጠት እንደሆነ ያወሱት የመሃል ዳኛው ሸለመ በቀለ፣ አቃቤ ህግ ለአራተኛ ጊዜ ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንዳቀረብ ጊዜ ይሰጠኝ በሚል ያቀረበው ጥያቄ ችሎቱ ያልተቀበለው በመሆኑ ውድቅ መደረጉን ገልፀዋል። ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያሉት ተከሳሾች እንዲሁም የ9ኛ ተከሳሽ ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ ለፍርድ ቤቱ የማመለክተው ነገር አለኝ በማለት ደምበኞቻቸው ላይ የቀረቡ ማስረጃዎች የተገኙት ከህግ አግባብ ውጪ መሆናቸውንና ደምበኞቻቸው ከተያዙ በኋላ የቀረቡ መሆኑንና ይህም የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 146 የተላለፈ መሆኑን ገልፀው አቃቤ ህግ ያቀረበው የሰነድ ማስረጃም ሆነ የሰው ምስክር ከክሱ ጋር ያልተያዘዘ መሆኑን ተረጋግጧል በማለት ሀሳባቸውን አጠቃለዋል። አቃቤ ህግ በበኩሉ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የሰነድ ማስረጃዎቹም ሆነ የሰው ምስክሮቻችን ውድቅ ሊሆኑ ይገባል ሲሉ ተጨባጭ ማስረጃ እንዳላቀረቡ ገልፆ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎችም ሆነ የሰው ምስክሮች ተቀባይነት ያላቸው መሆኑን አስረድቷል። አያይዞም የቀረቡት ‹‹የሰነድ ማስረጃም ሆነ የሰው ምስክሮች የቀረበውን ክስ ያስረዳሉ አያስረዱም የሚለው ፍርድ ቤቱ የሚመዝነው መሆኑን ገልፆ፣ ፍርድ ቤቱ የጠበቃ ተማም አባቡልጉን መቃወሚያ ወድቅ እንዲያደርገውና በተሰሙት የሰው ምስክሮችና በቀረቡት የሰነድ ማስረጃዎች ተገቢውን ብይን እንዲሰጠን እናመለክታለን›› በማለት ሀሳቡን አጠቃሏል፡፡
ፍርድ ቤቱ የዛሬው ችሎት ውሎ ከመቅረፀ ድምፅ ተገልብጠው ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ በማመልከት ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ለሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም ሰጥቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል በማሰብ የሚል ክስ የተመሰረተበት የአንድነት አባል የነበረው መሳይ ትኩ፣ በተመሳሳይ ሰአት ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ሲሆን ክስ መቃወሚያ ካለው ከጠበቃው ጋር በመሆን ሰኔ 26 ቀን 2007 ዓ.ም ይዞ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ ዜና በዘላለም ወርቅ አገኘሁ የክስ መዝገብ ስር የሚገኙት የቀድሞ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ፣ የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ም/ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺና የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል አፈጉባኤ የነበረው አቶ የሺዋስ አሰፋ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዞን ሶስት እንደተዘዋወሩ ለማወቅ ተችሏል፡:
tweet
One comment
Pingback: Court to give verdict on Public Prosecutor’s evidences Re: Zelalem Workagengehu et al. - EthioExplorer.com