De Birhan
July 08, 2013
Police Ena Ermejaw, a newspaper published by the Ethiopian Federal Police Commission has reported that an Ethiopian local official in Bugna Woreda, Amhara region, Belaynew Alemu, has been sentenced to a three years and three months rigorous imprisonment.
The official has reportedly embezzled over 10,000 birr collected for the building of the Great Ethiopian Renaissance Dam, to be built on Abay (Blue Nile) River, for his own personal use.
ለህዳሴው ግድብ የተሰበሰበውን ገንዘብ ለግል ጥቅሙ ያዋለው የቀበሌ ሥራ አስኪያጅ በእሥራት ተቀጣ
በዝናቤ በላይ
ለህዳሴው ግድብና ከእርሻ ግብር የተሰበሰበውን ገንዘብ ለግል ጥቅሙ ያዋለው የቡግና ወረዳ ቀበሌ ዐ4 ስራ አስኪያጅ በእስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
በአማራ ክልል የቡግና ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር እንግዳው ሆደነው እንደገለፁት ተከሳሹ በላይነው አለሙ ላይ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለው በህዳሴው
ግድብና በግብር የተሰበሰበውን 1ዐ ሺ 58ዐ ብር ለግል ጥቅሙ በማዋሉ ነው ብለዋል፡፡ እንደ ኃላፊው ንግግር ተከሳሽ በላይነው አለሙ በቡግና ወረዳ የዐ4 ቀበሌ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ በመሆኑና በዚሁ አጋጣሚ በእጁ የገባውን ብር ይዞ ወደ ትውልድ ሀገሩ ደቡብ ጎንደር ላይ ጋይንት በመሄድ በስሙ የባንክ ደብተር በመክፈት 6 ሺህ ብር አስቀምጦ ቀሪውን እንዳጠፋው ነው የሚገልፁት፡፡ ኃላፊው አክለውም ተከሳሹ የካቲት 2ዐ ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም የትምህርት ማስረጃውን ለመውሰድ ቡግና ወረዳ ቀበሌ
ዐ4 መግባቱን የተመለከቱ ሰዎች ጥቆማውን ለፖሊስ በመስጠታቸው በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን ጠቅሰው ምርመራውን በሰውና በሰነድ ማስረጃ አጠናክረው
ለሚመለከተው የፍትህ አካል ተልኮ ነበር ብለዋል፡፡ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ሚያዝያ 18 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም
በላሊበላ ከተማ ባስቻለው ችሎት ተከሳሽ በላይነው አለሙን በ3 ዓመት ከሶስት ወር የእስራት ቅጣት ወስኖበታል ሲሉ ኢ/ር እንግዳው ሆደነው ገልፀዋል፡፡
Source : Police ena Ermejaw Newspaper of the Ethiopia Federal Police
tweet