12-7-2016
In a statement read on State Television, the Ethiopian government has today announced that three key officers of the The Ethiopian National Intelligence and Security Service and Federal Police Counter-Terrorism Joint Taskforce, have been killed and five more wounded in North Gonder, Ethiopia last week when they attempted to arrest the suspected members of, what it called, “a terrorist and anti-peace organisation that is backed by the Eritrean government and a third country.”
The so called killers have not yet been apprehended except some suspects, the statement added.
The statement did not mention the name of the organisation it claimed was behind executing its members. The Force added that the suspected individuals have been receiving financial and weapon assistance from “terrorist and anti-peace forces based in Eritrea and a third country.”
ሐምሌ 5፣2008
በሰሜን ጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በኤርትራና በተለያዩ የውጭ ሃገራት ከሚገኙ አሸባሪና ከፀረ ሰላም ሐይሎች ጋር በመቀናጀት የተለያዩ የግድያና የአፈና ተግባር ሲያከናውኑ በቆዩ ተጠርጣሪ ወንጀሎኞች ላይ ረጅም ጊዜ የፈጀ ክትትል ሲደረግና ተጨባጭ ማስረጃ የማሰባሰብ ሥራ ሲሰራ ከቆየ በኋላ ከፍርድ ቤት ህጋዊ የመያዣ ፍቃድ በማውጣት የፌዴራል ፖሊስ ልዩ የፀረ ሽብር ቡድን በዛሬው ዕለት እርምጃ ወስዷል፡፡
ኤርትራና በሌሎች የውጭ ሃገራት ከሚገኙ አሸባሪና ፀረ ሰላም ሃይሎች የጦር መሳሪያ ገንዘብና መመሪያ እየተቀበሉ ሲንቀሳቀሱ የቆዩት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ወንጀለኞች ሲፈጽሟቸው ከቆዩት በርካታ ወንጀሎች መካከል ሰኔ 07/2008 አንድ ሰላማዊ ዜጋ በማፈንና በማገጽ ከቤተሰቦቹ በርከት ያለ ገንዘብ ለመዝረፍ ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ሰኔ 21/2008 በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዳንሻ ከተማ ጨለማን ተገን በማድረግ በጦር መሳሪያ አንድ ሰው ገድለዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በዚህ ወር በተለያየ ጊዜ በጠገዴ ወረዳ ጉርቢና ሰርቆ በተባሉ አካባቢዎች የተንቀሳቀሱ በመንግስትና ህዝብ ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርሱ የቆዩ ሲሆን ከኤርትራና ከሌላ የውጭ ሃገር በሚሰጣቸው የተለየ ዓይነት ድጋፍ እየታገዙ ለተከታታይ የአፈናና የግድያ ተግባር እራሳቸውን በከፍተኛ ደረጃ በማደራጀት ላይ የነበሩ ናቸው፡፡
በዚህ መሠረት የብሔራዊ መረጃና የደህንነት አገልግሎት እና ፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብር ሃይል ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ ለማቅርብ በወሰነው መሠረት አብዛኞቹ በዚሁ ተከታታይ የሆነ የአፈናና የግድያ ተግባር ላይ ተሰማርተው የቆዩት ተጠርጣሪዎች ወንጀለኞች ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ሲደረግ ሁለቱ ግን አሻፈረን በማለት በህግ አስከባሪዎች ላይ ተኩስ በመክፈት አደጋ አድርሰዋል፡፡
በህግ አስከባሪዎች ላይ ተኩስ ከከፈቱት ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ወንጀለኞች መካከል አንዱ በመኖሪያ ቤቱ የነበረውን ሰው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተኩሶ በመግደል መሽጎ ከነበረበት ቤት በማምለጥ ለጊዜው ተሰውሯል፡፡
ሁለተኛው ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ቤተሰቡንና ልጆቹን በጋሻነት አግቶ በመያዝ ተጠርጣሪው ወንጀለኛውን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተሰማራው የፌዴራል ፖሊስ ልዩ የፀረ ሽብር ቡድን በቤተሰቡና በልጆቹ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ባሳየው ገደብ የለሽ ትእግስት ምክንያት ተጠርጣሪው ወንጀለኛው አጋጣሚውን ተጠቅሞ በተኮሰው ጥይት አንድ የልዩ ፀረ ሽብር ቡድን አባል የተገደለ ሲሆን ይኸው ተጠርጣሪ ወንጀለኛ የተፈጠረውን ግርግር በመጠቀም ለተባባሪዎቹ የድረሱልኝ መልእክት ተጠርጣሪ ተባባሪዎቹ ከየነበሩበት ተጠራርተው በመምጠት ፎቅ ላይ በመውጣት በተኮሱት ተኩስ በሁለት ተጨማሪ የልዩ አባል ቡድን አባላት የሞት በሌሎች አምስት አባላት ላይ ደግሞ የማቁሰል ጉዳት አድርሰዋል፡፡
በፌዴራል ደረጃ የሚፈጸምን ወንጀል የመከላከልና የመክሸፍ ኃላፊት የተሰጠው የፌዴራል መንግስታዊ አካል በማንኛውም የአገሪቱ አካባቢ የህዝብን ንብረትና ህይወት የመከላከልና የመጠበቅ ስልጣን የተሰጠው ቢሆንም ለህግ አስከባሪ ሐይሎች እጃችንን አንሰጥም በማለት አሻፈረን ባሉ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ቤተሰብና ልጆች ላይ አደጋ እንደይደርስ ባሳዩት ከልክ ካለፈ ትእግስት ምክንያት ለኦፕሬሽኑ የተሰማሩ ሶስት የፌዴራል ፖሊስ ልዩ የፀረ ሽብር ቡድን አባላት ህይወታቸውን አሳልፈው ለመስጠት የተገደዱበት ሌሎች አምስት የህግ አስከባሪ አባላት ደግሞ የቆሰሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ችሏል፡፡
በዚህ ትእግስትና ጥንቃቄ የተሞላበት ህጋዊ እርምጃ ምክንያት በጀግንነትና በከፍተኛ የሙያ ዲስፕሊን ክቡር ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡት የፌዴራል ፖሊስ ልዩ የፀረ ሽብር ቡድን አባላት ታሪክ ለዘላለም የሚዘክራቸው ሲሆን ለዚህ አጋጣሚ እስካሁን ባለው መረጃ በተፈጠረው ግርግር በባራሪ ጥይት የአንድ ሰው ህይወት ከማለፉ በቀር በሰላማዊ ሰው ህይወትም ሆነ ንብረት ላይ የደረሰ ሌላ ጉዳት የለም፡፡
ከኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶችና የእነሱ ተላላኪ በሆኑ አሸባሪዎችና ፀረ ሰላም ኃይሎች በሚሰጣቸው መመሪያና የተለያዩ ዓይነት ድጋፍ የአገራችን ሰላምና አንድነት ለማናጋት የሚንቀሳቀሱ ወንጀለኞች መቼም ይሁን የትም ከህግ እንደማያመልጡ በዚህ አጋጣሚ በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን ሲል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረሃይል በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
Source: Ebc.com