በደስታዉ ሙላቴ
በሪፖርተር ጋዜጣ፣በተለያዩ ድህረ ገፆች እና በአንዳንድ የኤፍ ኤም(fm)ማሰራጫ ጣቢያዎች 40 እና ከአርባ በላይ የሚሆኑ የፌደራል ፖሊስ የታጠቀ ሀይል መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በክልሉ ፖሊስ ሃይል በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ለህብረተሰባችን ያሰራጩት መረጃ ከእዉነት የራቀና መሰረተ ቢስ ወሬ መሆኑን ስለ ጉዳዩ የሚከታተሉት የፖሊስ አመራር ገልፀዋል፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀረሽብርና የተደራጁ ወንጀለኞች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር አበራ ሁንዴ እንደገለፁት ተጨባጭ ባልሆነ መንገድ እንደነዚህ አይነት መሰል አሉባልታ ወሬችን እዉነታ በማስመሰል ለህብረተሰቡ በማስተላለፍ በኩል ከዚህ በፊትም በተለያዩ ድረ ገፆች ሲፈፅሙ የነበረ መሆኑን ጠቁመዉ፤ ሰሞኑንም ቢሆን አንዳንዶች የፌደራል ፖሊስ የኤርፖርት ጥበቃ አባሎች ሌሎች ደግሞ የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ሀይል በማለት የተለያዩ ስያሜዎችን እየሰጡ ወደ ግዳጅ የተላከን የፖሊስ ሀይል ለሌላ ተልዕኮ እንደሄደ በማስመሰል እና በዚህም ምክኒያት በክልሉ ፖሊስ ታግተዉ ምርመራ እየጠጣራባቸዉ መሆኑን የተላለፈዉ መረጃ ከእዉነት የራቀ መሆኑን ህብረተሰባችን ሊረዳዉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ረ/ኮሚሽነር አበራ ሁንዴ አያይዘዉ እንደገለፁት በአሁኑ ሰዓት እንደ ሀገር መንግስት መሰረታዊ ለዉጦችን ለማምጣት ሲል በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል::
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአሁን በፊትም ከክልል የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት ሲሰራ የነበረ ቢሆንም የበለጠ ለማጠናከር በአሁኑ ስዓትም የፖሊስ ሀይሉን ወደ ክልሎች በመላክ የህዝቦችን ሰላም እና ደህንነት እያስጠበቀ እንደሚገኝ ረ/ኮሚሽነሩ ተናግረዋል:: በቅርቡም በትግራይ ክልል ያለን የፀጥታ ሀይል ለማገዝ እና ችግሮች ከመፈፀማቸዉ በፊት የቅድመ መከላከል ስራ ለመስራት ይቻል ዘንድ የተላከን የፌዴራል ፖሊስ ሀይል አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ መንገድ ትርጓሜ በመስጠት የተላለፈዉ መረጃ ከእዉነታ የራቀ መሆኑን ግንዛቤ ሊኖር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ስለሆነም ህብረተሰባችን ሊረዳዉ የሚገባ ነገር ካለዉ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ሰራዊቱ ፈጥኖ መድረስ እንዳለበት በመታመኑ ወደ ቦታዉ በፕሌን እንዲሄዱ ተደርጓል::ይህ ወደ ቦታዉ የሄደን የፌዴራል ፖሊስ ሀይል የክልሉ ፖሊስ የሚያዉቀዉ እና በአሁኑ ሰአትም እንደ ተባለዉ ሳይሆን ያለምንም ችግር የተሰጣቸዉን ግዳጅ እየፈፀሙ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊዉ ለሌሎች ግዳጆችም ቢሆን እስታንድባይ በመሆን እገዛቸዉን እያደረጉ ያሉ እንጂ ለክልሉ ስጋት የሚሆን የተለየ እንቅስቃሴ ሊያደርጉ አለመሄዳቸዉን ልንረዳ ይገባል ሲሉም አክለዉ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ሀላፊዉ እንደገለፁት ዳይሬክቶሬቱ ዘርፈ ብዙ ተልዕኮዎችን የሚያከናዉን የስራ ክፍል እንደመሆኑ መጠን ስራዎቻችን ዉጤታማ እንዲሆኑ አመራሩ እና አባላት ከማንኛዉም የፖለቲካ ፓርቲ ነፃ መሆን ግድ በመሆኑ መግባባት ላይ የተደረሰበት ሁኔታ ላይ ይገኛል::ከዚህም በመነሳት ሰራዊቱ የተሰጠዉን ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ አክለዉ ገልጧል፡፡ በተመሳሳይ በስልክ ያገኘናቸው የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮ/ር ሙሉ ደሞዝ እንደገለፁት የፌዴራል ፖሊስ ለክልሉ ፖሊስ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አለም አቀፍ ኤርፖርት ታግተው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው ተብሎየዘገበው ሚዲያ የውሸት ዘገባ እንደሆነ ገልፀዋፈል፡፡
Source: ፖሊስና ርምጃው






