አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 9፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ብሄራዊ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ ገፅ እና በሞባይል አጭር የፅሁፍ መልዕክት ከዛሬ ጀምሮ ማወቅ ይችላሉ።
በዚህም መሰረት በኤጀንሲው ድረ ገፅ www.neaea.gov.et በመግባት ማወቅ እንደሚችሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ብሄራዊ ፈተናውን 246 ሺህ 570 ተፈታኞች የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 50 በመቶዎቹ 350 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል።
106 ተፈታኞች ደግሞ 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 21ዱ ሴቶች ናቸው።
ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥቡ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንም ኤጀንሲው አስታውቋል።





