Taffara Deguefe, who was Governor of the National Bank of Ethiopia in the early 1970s, has passed away.
የኢትዮጵያ ባንክ ገዥ የነብሩትና ለርዥም ዓመታት ሃገራቸውንና ህዝባቸውን በሙያቸው ያገለገሉት አቶ ተፈራ ደገፌ በቫንኩቨር-ካናዳ በህክምና ሲርዱ ከቆዩ ብኋላ በ88ዓምታችው ዛሬ አርብ ማርች 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 11 ሰዓት ተኩልከ (5፡30 am) ማርፋቸው ታወቀ።
አቶ ተፈራ በንጉሱ ዘመን በውጭ ሀገር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከተላኩት ጥቂት ተማሪዎች አንዱ ሲሆኑ በወቅቱ እርሳቸውና በጓደኞቻቸው ጥረት የተቋቋመው የውጭሃገር ተማሪዎች ህብረት የመጀመሪያውሰብሳቢ የነበሩና በቀጣይ አመት ግርማሜ ንዋይ ስልጣኑን እንደተረከበ ማስታወሻቸው ያወሳል። አቶ ተፈራ ደገፌ የባንክ ገዥ ሆነውባገለገሉበት ወቅት በርካታ አለማቀፍ ድርድሮችን ከመንግስታትና መንግስታዊ ያልሆኑ ታላላቅ አለማቀፍ ተቋማት ጋር በማድረግ ሀገራቸው በአለማቀፍ ደረጃ እውቅናእንድታገኝ በርካታጥረቶችን ከርማድረጋቸውም በላይ ንጉሱ ጋር የመቅረብ እድል ባገኙ ቁጥር ሃገሪቱን በተሻለ ጎዳና እንድታመራ ምክር ይሰጡ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የደርግ መንግስት ገንዘብ ለመቀየር ታስቦ በነበረበት ወቅት ገንዘቡ የኮሚኒስት ሃገራት እንዲታተም ሃሳብ በቀረበበት ወቅት አቶ ተፈራ አሳማኝ ያሉትን ሃሳብ ካቀረቡ ብኋላ ይህእሳቸው በስራ ላይ እያሉ ሊሆን እንደማይችልና መልቀቂያ እንዲሰጣቸው እስከመጠየቅ እንደደረሱ ለዚህም ሊቀምንበር መንግስቱ ጋር ቀርበው ሊቀመንበሩን በማሳመንእንግሊዝ ሃገር እንዲታተም ከማድረጋቸውም በላይ ምስጢሩ ሊቀ መንበሩን ጨምሮ 5 ሰዎች ብቻ እንዲያውቁት በማድረግ በከፍተኛ ምስጢር የገንዘብ ቅየራውን አንደፈጸሙይታወቃል። ገንዘቡ ሲታትም በአዲሱ የኢትዮጵያ ብር ላይ ፊርማቸው እንዲቀመጥ የተደርገ ቢሆነም ገንዘቡ በታተመ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ እስር ቤት መጣላቸውለብዙዎች መደናገርን ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።
አቶ ተፈራ ደገፌ በካናዳ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት የሚሰሩ ሁለት ልጆቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በመጭው ማክሰኞ ጠዋት የፍታትስነስርአት በምስካ ኅዙናን መድኀኒአለም እና ጸደንያ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከተደረገ በኋላ የቀብር ስነስርአታቸው እንደሚፈጸም ለማወቅ ተችሏል።
Here are further details about the memorial service and burial:
The memorial service will be held on
Tuesday March 10, 2015 at
ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም እና
ጸደንያ ቅድስት ማሪያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
628 Royal Avenue in New Westminster
from 9:00am – 1200pm.
His burial will be at the
Mountain View Cemetery in Vancouver
(5455 Fraser Street)
from 1:00pm – 1:30pm
After the burial, the memorial meal (ጸበል ጸዲቅ) will be at the
Celebration Hall of the cemetery
[Google]




