De Birhan » አማርኛ ፅሑፎች http://debirhan.com News and Analysis Site Horn of Afrique Thu, 31 Oct 2013 16:26:42 +0000 en-US hourly 1 http://wordpress.org/?v=3.5.1 ለስኳር ፋብሪካ ግንባታ እየተባለ ከህዝብ ካዝና የሚወጣው በጀት በኢህአዴግ ባለስልጣናት እየተዘረፈ ነው: ትሕዴን http://debirhan.com/?p=3004 http://debirhan.com/?p=3004#comments Thu, 17 Oct 2013 17:49:45 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=3004 17 October 2013

በሃገሪቱ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀችት እየተባለ በየዓመቱ የሚመደበው በጀት ለሚፈለገው ስራ ሳይውል በስርዓቱ ባለስልጣንት ይዘረፋል፣ በሚኒስትር ማእረግ የስኳር ኮርፖሬሽንን ሲመራ የነበረ አባይ ጸሃየ ከ 150 ሚልዮን ብር በላይ መዝረፉን ከደረሰን ዘገባ መረዳት ይቻላል፣ አባይ ጸሃየ በሰራው ወንጀል ተከሶ ወደ ፍርድ መቅረብ ሲገባው መ/ቤትን በመቀየር ወደ ሌላ የስራ መመደቡ ያልተዋጠላቸው የኮርፐሬሽኑ ሰራተኞች ዝውውሩን በመቋወም በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ገልጸዋል፣ በወልቃይት እየተገነባ ላለው ይስኳር ፋብሪካ ተብለው የሚላኩ የህንጻ መሳሪያዎች በተደጋጋሚ እንደሚዘረፉ መዘገባችን የሚታወስ ነው::

Source : TPDM

]]>
http://debirhan.com/?feed=rss2&p=3004 0
በሑመራ ከተማ ወጣቶችን በውትድርና ሞያ ለመመልመል በእህአዴግ ስርዓት ካድሬዎች ሰፊ ቅስቀሳ የተካሄደ ነው፣ http://debirhan.com/?p=2906 http://debirhan.com/?p=2906#comments Tue, 08 Oct 2013 20:22:57 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=2906 በደረሰን ዘገባ መሰረት በሑመራ ከተማ ከ 18-22 የእድሜ ክልል የሚገኙ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ተማሪዎች ውትድርና  እንዲመለመሉ ቅስቀሳ እየተደረገ ሲሆን ፥ የስርዓቱ
ካድሬዎች ውትድርናን የተመለመለ የትምህርት ደረጃው እየታየ በኮምፒዩተር ፤ በመካኒክና ሌሎች ሞያ እንዲሰለጥን ይደረጋል የሚል የማይተገበር ቃል እየገቡ ወጣቱን ለማታለል
ቢሞክሩም ወጣቶቹና ቤተሰቦቻቸው ግን ቅስቀሳ ለማዘናጋት የሚደረግ የተለመደ ነገር መሆኑን በመገንዘብ ውድቅ ማድረጋቸውን ለመረዳት ተችሏል፣ ከዚህ ቀደም ባቀረብነው የዜና ዘገባ በመከላከያ ሰራዊት የብሄረ ትግራይ ተወላጆች ቁጥር በተለያየ ምክንያት እየተመናመነ ስለመጣ በልዩ የምልመላ አሰራር ከክልሉ ወጣቶችን ለመመልመል እንቅስቃሴ መጀመሩን ዘገባባችን የሚታወስ ነው::

Source : ትህዴን

]]>
http://debirhan.com/?feed=rss2&p=2906 1
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት አቆሙ http://debirhan.com/?p=2883 http://debirhan.com/?p=2883#comments Fri, 04 Oct 2013 23:31:46 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=2883 መስከረም ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከአስተዳደሩ ጋር የብቃት መመዘኛ ፈተና ዙሪያ መግባባት ባለመቻላቸው ትምህርት ማቆማቸው ተሰማ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስተላለፈው ውሳኔ በተማሪዎቹና በዩኒቨርሲቲው መካከል አለመግባባትን በመፍጠሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ የዩኒቨርሰቲውም የአራተኛ ዓመት ተማሪዎች ግቢ ለቀው መውጣታቸውን ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ተማሪዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብቃት ማረጋገጫ እንዲወስዱ ሲጠይቃቸው ተማሪዎቹ በቂ የዝግጅት ጊዜ ይሰጠን ብለው በመጠየቃቸው አለመግባባቱ ተከስቷል፡፡

የብቃት ማረጋገጫ ፈተናውን ለመውሰድ በቂ ጊዜ ይሰጠን ብለን ብንጠይቅም ዩኒቨርሲቲው በአጭር ቀናት ውስጥ እንድንወስድ አስገድዶናል በማለት ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ለሶስት ዓመት ያህል የተማሩትን ትምህርት በቂ ዝግጅት ሳያደርጉ በሁለት ቀናት ውስጥ የብቃት መመዘኛውን ውሰዱ መባሉ አግባብነት የሌለው ነው የሚሉት ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ግን ሙሉ ለሙሉ መፈተን እምቢ እንዳልን አስመስሎ በመግለጽ ላይ ነው ሲሉ ተማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡

በተማሪዎቹና በአስተዳደሩ የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ፌደራል ፓሊስ ያደረገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ተማሪዎች ግቢውን ጥለው መውጣታቸው ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ በአምስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ በአክራሪነትና ፅንፈኝነት ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት የተዘጋጀ ፕሮግራም ባለመግባባት መበተኑን ምንጮች ለኢሳት አስታውቀዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በአክራሪነት ዙሪያ ለመወያየት ፈቃደኝነታቸውን ማሳየት ባለመቻላቸውና ሙስሊም ተማሪዎች ለጁማ ሶላት መውጣት በመሞከራቸው በግዳጅ ወደ ስብሰባ እንዲሄዱ ተሞክሮ እንደነበር ታውቋል፡፡

ESAT

]]>
http://debirhan.com/?feed=rss2&p=2883 0
የትህዴን ደጋፊዎች ግንቦት-7 እያካሄደው ባለ ስብሰባ መገኘታቸውን የትህዴን የህዝብ ግንኝነት ገለጸ http://debirhan.com/?p=2864 http://debirhan.com/?p=2864#comments Fri, 04 Oct 2013 16:23:34 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=2864 ትህዴን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኘው ግንበት-7 ጋር ተባብሮ  ለመስራት መግባባት ላይ ከመድረሱም በላይ በተግባር በተለያየ መልኩ ሲተጋገዙ የቆዩ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ  የትህዴን አ ባላት የጉንበት-7 አ መራር ከአ ባላቱ ጋር በተለያዩ ሃገራት እያካሄደው ባለ ስብሰባ በመገኘት አንድነታችንን አ ጠናክረን እጅ ለእጅ
ተያይዘን እንሰራለን ሲሉ ለግንበት-7 ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን  የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣ በስብሰባው የተገኙ የትህዴን ተወካዮች አ ያይዘው እኛ በዚሁ ስብሰባ
ስንገኝ ለይምሰል ሳይሆን የህዝብን ድምጽ በAፈሙዝ ረግጦ ስልጣን  የተቆናጠጠውን ከፋፋዩን የእህAዴግ ስርዓትን በሚገባው ቋንቋ በትጥቅ ትግል ከስሩ መንግሎ ለመጣል ገና ከመነሻው ትህዴን አ ምኖበት የተነሳለት በመሆኑ የድርጅቱን ዓላማ እግቡ ለማድረስ የሁለቱም ድርጅቶች Aባላትና ደጋፊዎች የIህአ ዴግ ስርዓት መለያ ከሆነው በዘር የመከፋፈል Aባዜ በመውጣት በሙሉ ልብ ድርጊቱን በማውገዝ ከሃገር ውስጥ ይሁን ከሃገር ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከመቸውም ጊዜ በላይ ግንኝነታችንን አጠናክረን ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፣ የግንበት-7 አመራርናአ ባላት በቡኩላቸው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች በመሳሪያ ፤ በሰው ሃይልና በዓላማ ሲታይ ትህዴን ንካራ መሆኑን በመግለጽ እንዲህ ካለው Aስተማማኝ ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት አልፈን አ ብረን እየሰራን ነው፣ ይህ መልካም ጅምር አጠናክረን እንቀጥልበትአለን ሲሉ ገልፇል::

Source: ትህዴን

]]>
http://debirhan.com/?feed=rss2&p=2864 0
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ28 ሩዋንዳዊያን ነጻ የትምህርት እድል ሰጠ http://debirhan.com/?p=2843 http://debirhan.com/?p=2843#comments Wed, 02 Oct 2013 21:39:44 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=2843 አርባምንጭ መስከረም 22/2006 የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው የትምህርት ዘመን ከኢትዮጵያዊያን መደበኛ ተማሪዎች ጋር ለሚማሩ 28 ሩዋንዳዊያን ዘጎች የትምህርት እድል መፍቀዱን አስታወቀ። በዩኒቨርሲቲው የኮርፖሬት ኮሙኒከሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገነነ ገደቡ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ለሩዋንዳዊያን የትምህርት እድል ሲፈቅድ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት እ.ኤ.አ በ2010 በኢትዮጵያ ደረጃ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ብቻ በሚሰጠው በአየር ትንቢያ ትምህርት ክፍል እንዲማሩ የተፈቀደላቸውን ሰባት ራዋንዳዊንን ባለፈው ሐምሌ ወር በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቆ መሸኘቱንም ገልጸዋል። በዘንድሮ ትምህርት ዘመን ለሁለተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲው የመማር እድል ካገኙ ሩዋንዳዊን መካከል 14ቱ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 12ቱ በማስተርስ ዲግር እንድማሩ እንደተፈቀደላቸው ገልጸው ሁለቱ ደግሞ በዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚከፍተው በመስኖ ምህንድስና በዶክትሬት ዲግር እንዲማሩ እንደተፈቀደላቸውም ተናግረዋል። ሩዋንዳዊያኑ ከኢትዮያዊያን ወንድሞቻቸው ጋር በመማራቸው የሁለቱ ሀገሮች የቆየውን የሁለትዮሽ መልካም ግንኙነትና ትብብራቸውን ከማጎልበቱም በላይ የሀገሮቹን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከማጠናከር አንጻርም ፋይዳው የጎላ እንደሆነም አቶ ገነነ ገልጸዋል። አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥሉት 15 ዓመታት ውስጥ በውሃው መስክ በምስራቅ አፍርካ የልቀት ማዕከል ለመሆንና በአፍርካና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳዳሪ ለመሆን ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ከዚህ አንጻርም ዩኒቨርሲቲው የውጭ ዜጎችን በመማር ማስተማሩ እያሳተፈ እንደሚቀጥል አቶ ገነነ ጨምረው ተናግረዋል።

]]>
http://debirhan.com/?feed=rss2&p=2843 0
በአንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ የተሠጠ ጋዜጣዊ መግለጫ http://debirhan.com/?p=2785 http://debirhan.com/?p=2785#comments Sat, 28 Sep 2013 16:20:41 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=2785   አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)             

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

    በማሰርና ማደናቀፍ የታጀበው ሰላማዊ ሰልፋችን በታቀደለት ዕለት በድምቀት ይካሄዳል!!

 አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለሶስት ወራት የሚቆይ ህዝባዊ ንቅናቄ በስትራቴጅው መሰረት በመጀመር፤ በመላው አገሪቱ የሚገኙ አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን በማንቀሳቀስ ሕዝቡን ያሳተፈ ትግል በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችንና ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማከናወኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የሚልዮኖች ድምጽ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ይህ ህዝባዊ ንቅናቄ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን ያነገበ ሲሆን እንደ ሁልጊዜውም ፓርቲው ሰላማዊነቱን በጠበቀ መልኩ ነገር ግን ሕጋዊ መብቱን ሳያስነካ፤ መከፈል የሚገባውን መስዋዕትነት በመክፈልና በቁርጠኝነት ንቅናቄውን በታቀደለት መሰረት ከአባላቱና አመራሩ ጋር በመሆን ለማከናወን ችሏል፡፡

አገሪቱን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ገዥ ሀይል በሰላማዊ ህዝባዊ ንቅናቄዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠትና በተነሱ ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር በርን ከመክፈት ይልቅ ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ ለጥያቄዎቹ አስተጋቢዎች የተለየ መልክ ለመፍጠር የሚያደርገው ሩጫ እንደተጠበቀ ሆኖ በህገ መንግስቱ በግልጽ የተቀመጡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ የመሰብሰብና አቤቱታ የማቅረብ መብትን በአደባባይ እየጨፈለቀና እነዚህ መብቶች ይከበሩ ዘንድ የሚጠይቁ አባላቶቻችንን ከህግ አግባብ ውጪ በገፍ እያሰረም ቢሆን ህዝባችን ጋር ለመድረስና ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን ማሰማት ችለናል፡፡

በጎንደርና ደሴ ከተማ በ7/11/2005 የጀመርናቸው የተቀውሞ ሰልፎች በባህርዳር፣ በአርባምንጭ፣ በጅንካ፣ በአዳማ፣ በፍቼ በተሳካ ሁኔታ የተካሄዱ ሲሆን በመቀሌና ባሌ ሮቤ በከፍተኛ ጫናና ህገወትነት ሳካሄዱ ቀርተዋል፡፡ በወላይታ ሶዶና አዲስ አበባ ህዝባዊ ስብሰባዎች ተከናውነዋል፡፡

ከላይ በጠቀስናቸው ከተሚች ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማሰናከል ሃላፊዎቹ የየአካባቢዎቹን ሚሊሻዎች፣ የደንነት ሰዎች፣ ታጣቂዎችና ፖሊሶች በመጠቀም አባላቶቻችንን አስረዋል፣ አስፈራርተዋል፣ ደብድበዋል፣ አዋክበዋል፡፡  ከአንድ የመንግስት አካል በማይጠበቅ መልኩም አመራሮቻችንን አግተዋል፣ የተለጠፉ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ወረቀቶችን እንዲቀደዱ በማድረግና ህዝቡ በሰልፎቹ እንዳይገኝ በካድሬዎች አማካኝነት የቤት ለቤት ቅስቀሳ ከማካሄዳቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዳይኖር በማድረግ ከየከተሞቹ አቅራቢያ ከሚገኙ ወረዳዎች ዜጎች ድምጻቸውን ለማሰማት እንዳይመጡ እንቅፋት ፈጥረዋል፡፡           በተንቀሳቀስንባቸው አካባቢዎች ሁሉ ገዢው ፓርቲ ከህዝብ የተነጠለ መሆኑንና ህዝቡን እየመራሁ ነው የሚለው ህዝብን በማሸማቀቅ እንደሆነ መገንዘብ ችለናል፡፡

የመጀመሪው ዙር የሶስት ወር ሕዝባዊ ንቅናቄችን ከ33ቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ እንደሚጠናቀቅ በገለፅነው መሰረትም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችንና ዝግጅቶቸን ስናደርግ ቆይተናል፡፡ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 3ዐ ተራ ቁጥር (1) መሰረት ዜጎች የመሰብሰብና በጋራ ሠላማዊ ሠልፍ ማድረግ እንደሚችሉ በተደነገገው መሠረት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በ24/12/2ዐዐ5 በተፃፈ ደብዳቤ ሕጉ የሚጠይቀውን አሟልቶ የተቃውሞ ሠላማዊ ሠልፍ መስከረም 5 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ለማድረግ መወሰናችንን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠላማዊ ሠልፍ ማሳወቂያ ክፍል  አሳውቀናል፡፡  ሆኖም በ12 ሰዓት ውስጥ መልስ  ባለማግኘታችን ስለ ጉዳዩ ለማጣራት ከመስተዳድሩ የከንቲባው ጽ/ቤት ኃላፊ ጋር ተገናኝተን ሠፊ ውይይት ካደረግን በኋላ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ በወቅቱ በመስቀል አደባባይ ለግንባታ ሥራ ተብሎ አካባቢው በቆርቆሮ የታጠረ ስለሆነ ጊዜ ተገኝቶ ቆርቆሮዎቹ ተነስተው ለጥበቃ አመቺ እስከሚሆን ድረስ የሠላማዊ ሠልፉ ከመስቀል በዓል በኋላ እንዲደረግ ስለጠየቁንና እንዲሁም  የትምህርት ቤቶች  መክፈቻ ወቅት ከመሆኑም በተጨማሪ በአካባቢውም ከአዲስ ዘመን መለወጫ ጋር በተያያዘ ብዙ ባዛሮች የሚስተናገዱበት ጊዜ በመሆኑ ጊዜው እንዲለወጥ የሚሉ ምክንያቶች በመቅረባቸው  በመስቀል አደባባይ ለማድረግ የማንችል መሆኑን ቢነግሩንም በአደባባዩ ግን፡-

1ኛ.  ነሐሴ 19 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት ምክንያት በማድረግ ሕዝባዊ ስብሰባና ሠላማዊ ሠልፍ የተካሄደበት መሆኑ፤

2ኛ. ነሐሴ 26 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም የኢትዮጵያ የኃይማኖቶች ተቋማት ጉባኤ ሠላማዊ ሠልፍ  እንዳካሄዱበት እየታወቀ የተሰጡን ምክንያቶች ውሃ የማይቋጥሩና አድሏዊ መሆናቸውን ብናምንም ሆደ ሰፊ በመሆንና እስከመጨረሻው ለመሄድ በማሰብ ሠላማዊ ሠልፉ ወደ መስከረም 19 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም  እንዲተላለፍ አድርገናል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የከንቲባው ጽ/ቤት መስከረም 3 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሠላማዊ ሠልፉን መስከረም 19 ቀን ማድረግ እንደምንችል  ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ቅጽ  ሲያሳውቀን  በቅፁ ላይ መሠረታዊ የሆነውን የሠላማዊ ሠልፉን የመዳረሻ ቦታ ክፍት (ዳሽ) በማድረግ ቀደም ስንል የተስማማንበት ቦታ መስቀል አደባባይን ሳይጠቀስ ቀረ፡፡ ፓርቲያችንም ይህ ተገቢ ያለመሆኑንና የመስተዳድሩን ተዓማኒነት የሚያሳጣው ስለሆነ ሠላማዊ ሠልፉን በመስቀል አደባባይ እንድናደርግ እንዲወሰንልን በተደጋጋሚ ብናሳስብም ተወያይተን  መፍትሔ እንሰጣለን በማለት መልሱን በአስር ቀናት ከአዘገዩ በኋላ በቁ.አ.አ/ከጽ/1ዐ/3ዐ.4/12 ሠላማዊ ሠልፉን በጃንሜዳ እንድናደርግ መወሰኑን ገለፁልን፡፡  ሆኖም በዚህ ደበዳቤ መጨረሻ ላይ ‹‹… ከመስቀል አደባባይ ውጭ ሌላ አማራጭ ካላችሁ ማቅረብ እንደሚቻል እናሳስባለን›› ባሉት  መሠረት የፓርቲው አመራር በጉዳዩ ላይ ሠፋ ያለ ውይይት ከአደረገ በኋላ ከላይ በጠቀስናቸው ምክንያቶች  የተሰጠን መልስ በመስቀል አደባባይ ሠላማዊ ሠልፍ የማድረግ መብታችንን የጣሰ፣ የደፈጠጠ፣ ኢ-ፍትሓዊና አድሎአዊ መሆኑን ሙሉ በሙሉ ብናምንም አሁንም መስተዳድሩ እውነት ልማት አስጨንቆት ነው ወይስ ሰላማዊ ሰልፎችን በወረቀት ብቻ ዕውቅና በመስጠት ሌሎችን የማፈን ተግባር የሚለውን በተጨባጭ ለመፈተሽ የተፈቀደልን ጃንሜዳ በአዋጅ ቁጥር 3/1983 ዓ.ም  ለሠላማዊ ሠልፍና  የተከለከሉ ሥፍራዎች በሚለው አንቀጽ ሥር ‹‹ማንኛውም ሠላማዊ ሠልፍ ወይም ሕዝባዊ የፖለቲካ ስብሰባ በጦር ኃይሎች፣ በጥበቃና የሕዝብን ሠላምና ደህንነት በሚቆጣጠሩ የመንግሥት የሥራ ክፍሎች አካባቢ 5ዐዐ ሜትር ርቀት ውስጥ ሊደረግ አይችልም›› የሚለውን በመጥቀስ ጃንሜዳን የማንቀበልበትን ምክንያቶች አቅርበናል፡፡ በዚህም መሰረት፡-

ሀ) በጃን ሜዳ ዋና መግቢያ በር ፊት ለፊት የመከላከያ ዩኒቨርስቲ በመኖሩ፤

ለ) በጃን ሜዳ ሁለተኛ በር የቀድሞ 3ኛ ሻለቃ ማዕከላዊ እዝ በመኖሩ፤

ሐ) በጃን ሜዳ 3ኛ በር የአራዳና የየካ ክፍለ ከተማ የፌዴራል መምሪያ የሚገኙ  ስለሆነ  ይህን ሥፍራ ለሠላሚዊ ሠልፍ መፍቀድ አዋጅን የሚጥስ በመሆኑ ትክክል እንዳልሆነ እና እኛም የሕግ ጥሰት ተባባሪ መሆን ስለማንፈቅድ መስከረም 13 ቀን በተፃፈ ደብዳቤ አማራጭ ይሆናሉ ያልናቸውን፡-

  • ኢትዮ ኩባ አደባባይ ፊት ለፊት
  • አራት ኪሎ አደባባይን
  • ስድስሰት ኪሎ አደባባይ
  • ቴዎድሮስ አደባባይ
  • አብነት ሆቴል ፊት ለፊት ያለው አደባባይ
  • ሳርቤት አካባቢ ያለው ፑሽኪን አደባባይ
  • ብሔር-ብሔረሰቦች አደባባይ
  • አዲስ አበባ ስቴድዩም
  • በቦሌ ድልድይና በኢምፔሪያል ሆቴል መካከል ከቀለበት መንገድ ግራና ቀኝ ያለው ሜዳ  መሆናቸውን በመግለጽ ምላሽ በመጠባበቅ የቅስቀሳ ስራችንን በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሆነን እያከናወንን እንገኛለን፡፡

በቅስቀሳ ወቅትም ከማክሰኞ መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በእቅዳችን መሰረት ከ 33ቱ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ጋር በመሆን የመኪና ላይ ቅስቀሳ፣  በራሪ ወረቀ፣  ፖስተር መለጠፍ የጀመርን ቢሆንም የከተማው መስተዳድር ህግ በተላለፈ ሁኔታ ነሐሴ 10 ቀን 2006 ዓ.ም የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ የሚከለክል የውስጥ መመሪያ በማውጣት ፓርቲዎች፣ ምርጫ ቦርድና ሚደዲው ሳያውቅ በድብቅ ለአዲስ አበባ ፖሊስና ክፍለ ከተሞች በማሰራጨት አባሎቻችንና አመራሩ ለቅስቀሳ ሲወጡ እንዲታሰሩ አድርጓል፡፡

በዚህ ህገ-ወጥ መመሪያ የተነሳም ማክሰኞ መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ.ም ሦስት መኪናና አጠቃላይ 30 ቀስቃሽ አባላት ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ታስረው ከምሽቱ 1 ሰዓት ተለቅቀዋል፤ ዕሮብ መስከረም 16 ቀን 2006 ዓ.ም ሦስት መኪናና 28 ቀስቃሽ አባላት በተመሳሳይ ታስረው ማታ ተለቅቀዋል፤ ሐሙስ መስከረም 17 ቀን 2006 ዓ.ም ሁለት መኪናና 16 ቀስቃሽ አባላት የታሰሩ ሲሆን የፓርቲያችን ሊቀ መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የታሰሩትን ለማስፈታ ወደ ሽሮ ሜዳ ፖሊስ መምሪያ ቢሄዱም የታሰሩ አባላት ካልተለቀቁ አልሄድም በማለት አብረው ታግተው ውለዋል፡፡ መስከረም 18 ቀን 2006 ዓ.ም የፓርቲው መሪ፣ የስራ አስፈፃሚ አባላትና አመራሩ በሁለት መኪና በመሆን አንደኛውን መኪና ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እየመሩት፣ ሁለተኛውን መኪና የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ እየመሩት ቅስቀሳ ቢጀመርም አጠቃላይ 26 አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው እንዳይቀሰቅሱ ተደርጓል፡፡ ፓርቲያችን በተለያዩ መንገዶች ቅስቀሳውን ማድረግ አጠናክሮ በመቀጠል ሁለት መቶ ሺ በራሪ ወረቀቶች ተሰራጭተዋል፤ አስር ሺ ፖስተሮች ተለጥፈዋል፡፡ ሕዝቡም በነቂስ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፉን በመቀላቀል በሰላማዊ መንገድ የተቃውሞ ድምፁን እንዲያሰማ በአክብሮት ሀገራዊ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

በዚህም መሰረት መንግስት በወረቀት ብቻ እውቅና ሰጥቶ በተግባር ቅስቀሳ የከለከለ ቢሆንም የተቃውሞ ሰልፋችን በታቀደለት ዕለት ሠልፉ በምንም አይነት ጫና  የማይሰረዝ መሆኑን እያረጋገጥን  መነሻውን ከፓርቲያችን ፅ/ቤት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑን  እየገለጽን፤  አንድነት ለሠላማዊ ትግል የሚከፈሉ መስዋትነቶችንን  ከፍሎ  የትግላችንን ፍሬ እንደምናረጋግጥ  እርግጠኛ ብንሆንም በአሁኑ ወቅት መንግሥት በማከናወን ላይ ያለው ተግባር ከሠላማዊ ትግል ውጭ ያሉ አማራጮችን በቀጥታ እያበረታታና እየደገፈ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳልን፡፡  በመጨረሻም የመንግሥት ተግባር  መሠረታዊ  የሆነ  የዜግነትና የአገራዊ ባለቤትነት ጥያቄን ስለሚያስነሳ፤ አፈናው እንዲቆም በአገርና በሕዝብ ስም  እየጠየቅን ይህን ፍርደ ገምድልና ኢ-ፍትሓዊ ውሳኔን ተከትሎ ለሚደርሱ ችግሮች ተጠያቂው መስተዳድሩና መንግሥት መሆኑ እንዲታወቅ አበክረን እንገልፃለን፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለኢትዮጵያ!!!

የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች

መስከረም 18 ቀን 2006

አዲስ አበባ

UDJ

 

]]>
http://debirhan.com/?feed=rss2&p=2785 0
ከባድ የጦር መሳሪያዎችን የተሸከሙ መኪኖች ወደ ሰሜን ማቅናታቸው ተዘገበ http://debirhan.com/?p=2782 http://debirhan.com/?p=2782#comments Sat, 28 Sep 2013 07:56:58 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=2782 መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይን እማኞች እንደገለጹት ባለፉት 3 ቀናት ከ30 በላይ የሚሆኑ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ሰሜናዊ ክፍል አቅንተዋል።

መንግስት የጦር መሳሪያዎችን ለማንቀሳቀስ ለምን እንደፈለገ የታወቀ ነገር የለም። አንዳንድ ወገኖች እንደሚገምቱት በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አማጽያን የሚፈጥሩትን ስጋት ለመቋቋም ተብሎ የተወሰደ እርምጃ ሊሆን ይችላል።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለመነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም::

]]>
http://debirhan.com/?feed=rss2&p=2782 0
ህዝብና የመንግስት መሬት በህገ ወጥ መንገድ የቸበቸቡ አመራሮች በእስራት ተቀጡ http://debirhan.com/?p=2780 http://debirhan.com/?p=2780#comments Sat, 28 Sep 2013 07:50:49 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=2780 ርባምንጭ መስከረም 17/2006 በጋሞ ጎፋ ዞን በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ጋንታ ካንቻማ ቀበሌ ከ58 ሄክታር የሚበልጥ የህዝብና የመንግስት መሬት በመቸብቸብ ለራሳቸውና ለሌሎች ያከፋፈሉ የቀበሌው አመራር አባላት ከ2 እስከ 3 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የጋሞ አከባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ገለጸ። በቡድን ወረራ የተቸበቸበው 58 ነጥብ 5 ሄክታር የእርሻ መሬት ለህዝብና ለመንግስት ተመላሽ ሆኖ ለመሬት ባንክ ገቢ ተደርጓል። የጋሞ አከባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት አቶ በቀለ ባሻ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በመፍቀዳቸውና በመሳተፋቸው በማስረጃ ተረጋግጦባቸው የተቀጡት በወረዳው የጋንታ ካንቻማ ቀበሌ ሊቀመንበር ፣ ምክትል ሊቀመንበርና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ናቸው። የቀበሌው ሊቀመንበር በረደ ባርጉደ በቀበሌው በአገር በቀልና በውጭ ዝርያ ዛፎች የተሸፈነውን 58 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ለራሱና ለሌሎች አመራሮች በህገ ወጥ መንገድ በማከፋፈል በመሬቱ ላይ ያለው ደን በሰደድ እሳት እንዲቃጠል ማድረጉ በሰውና ሰነድ ማስረጃ ተረጋግጦበት መከላከል ባለመቻሉ በ3 ዓመት ከ2 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል። የቀበሌው ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ዘይራ ዘንባ ከቀበሌው ምክትል ሊቀመንበር ጋር በመሆን ቀሪውን መሬት በእርሻ ስራ ከማይተዳድሩና በከተማ ካሉ አንዳንድ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር በህገ ወጥ መንገድ መቸብቸባቸው በማስረጃ በመረጋገጡ እያንዳንዳቸው 1 ዓመት ከ 6 ወር እስራት እንዲቀጡ መወኑን ገልጸዋል። ፍርድ ቤቱ ሰሞኑን ባካሄደው ችሎት ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ መሬቱ ለህዝብና ለመንግስት ተመላሽ ሆኖ መሬት ባንክ እንዲገባ አብሮ መወሰኑን ተናግረዋል።

]]>
http://debirhan.com/?feed=rss2&p=2780 0
በደቡብ ክልል በ 2005 የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች 5% ብቻ አለፉ፣ http://debirhan.com/?p=2739 http://debirhan.com/?p=2739#comments Mon, 23 Sep 2013 23:11:03 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=2739 በክልሉ በአጠቃላይ በ 2005 ዓ/ም የት/ዘመን የ 10ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች 5% ብቻ ወደ መሰናዶ የሚያስገባ ነጥብ ያገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ 95% ተማሪዎች ፈተናውን ማለፍ አልቻሉም፣ በዚህ ዓመት የነበረው የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 2.7 ሲሆን ለሴቶች ደግሞ 2.29 ነበር ። በጣም በራቀ ገጠር አከባቢ ለሚገኙ ለሴቶች 2.14 ሲሆን ለወንዶች ደግሞ 2.4 ያመጡ ተማሪዎች ወደ የሚቀጥለው የመሰናዶ ትምህርት የመግባት እድል Aላቸው። ለ 95%  ተማሪዎች መውደቅ ዋና ምክንያት የስርዓተ ትምህርት ጥራት ችግር በዋናነት ይጠቀሳል::

TPDM

 

]]>
http://debirhan.com/?feed=rss2&p=2739 0
ሆዱን ያየ ሆዱን ተወጋ http://debirhan.com/?p=2735 http://debirhan.com/?p=2735#comments Mon, 23 Sep 2013 08:27:15 +0000 chebude22 http://debirhan.com/?p=2735 ይህ: ግጥም፡ለሆዳቸው: ሲሉ: ህሊናቸውን:በቆራጥነት: ለገበሩ: ወንድምና: እህቶች: መታሰቢያ: ይሁን:: ህዳሴ:ህዳሴ: ብሎ: ለፈለፈ:
ምድረ ሆዳም ሁሉ አሰፈሰፈ
ፍርፋሪ አገኝ ብሎ አነፈነፈ
ከዘረኞች ጋራ ባንዴ ተሰለፈ::
ስማ ሆዳሜ የአገር ሸክም:
ያገኘህ መስሎህ ጥቅማ ጥቅም
አትሯሯጥ አትቀላውጥ
ሀገር ህዝብህን አትሽጥ::
ህዳሴ ህዳሴ ብለው ሲነግሩህ
በደደቢት ቋንቋ ሲያጭበረብሩህ
አንተም አመነሃቸው እውነት መስሎህ
ተከትለህ ስትሮጥ ትንፋሽ እስኪያጥርህ
ትንሽ ባገኝ ብለህ ከሚዘረፈው
የህዝቡን መበደል ክደህ አረፍከው::
ታሪክህ ሲነገር ይኸ ዘመን አልፎ
የክህደትህ መጠን አያልቅም ተጽፎ::
ተው ተመለስ እባክህ ጊዜው ሳይረፍድ ብዙ
ለሆድ ብሎ ማደር ትልቅ ነው መዘዙ
ለትውልድ ይተርፋል ሸክሙና ጓዙ::
ታዛቢ

]]> http://debirhan.com/?feed=rss2&p=2735 0