የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማክሰኞ ህዳር 24 ቀን 2006 ኢትዮጵያውያንን ከሳዑድ አረቢያ የመመለሱን ሥራ ያለበትን ደረጃና እና የኢትዮ-ሱዳን 3ኛው የጋራ ኮሚሽን ሥብሰባ ጉዳዮች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ኢትዮጵያውያንን ከሳዑድ አረቢያ የመመለሱ ሂደት በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ በመሆኑ አሁን ባለው ሂደት መጓዝ ከተቻለ በሚቀጥለው ሣምንት ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያውያንን የመመለሱ ሂደት እንደሚጠናቀቅ አስታውቋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑድ አረቢያ የመመለሱ ሥራ በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ መሆኑን በመጠቆም እስከ ማክሰኞ ህዳር 25 ቀን 2006 ቀትር ድረስ፣ 93 ሺህ 6መቶ ኢትዮጵያውያንን ውደ ሀገራቸው መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ውስጥም 54 ሺህ 5 መቶ 29 ወንዶች፣ 28 ሺህ 9 መቶ 43 ሴቶች እንዲሁም 4 ሺህ 51 የሚሆኑት ደግሞ ህጻናት መሆናቸውን አምባሳደሩ አስታውቀዋል፡፡
አምባሳደር ዲና እንዳሉት አስከፊ የሆነውን ህገ – ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት በዋናነት ህብረተሰቡ፣ እያንዳንዱ ግለሰብ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት በመደገፍ እንዲንቀሳቀሱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እና ሱዳን 3ኛው የጋራ ኮሚሽን ሥብሰባ በኃይል፣ በንግድ፣ በቱሪዝም እና ተመሳሳይ መስኮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ ሥምምነቶች እንደሚፈረሙ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል ፡፡
አምባሳደር ዲና እንዳሉት የኢትዮ-ሱዳን የእርስ በእርስ ግንኙነት በምስራቅ አፍሪካ በምሳሌነቱ የሚጠቀስ በመሆኑ ይህን ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ 3ኛው የኢትዮ-ሱዳን የጋራ ኮሚሽን ሥብሰባ በሁለቱ ሃገራት የተለያዩ የመንግሥት አካላት መካሄድ መጀመሩንም ተናግረዋል፡፡
በ2ኛው የሀገራቱ የጋራ ኮሚሽን ሥብሰባ ላይ የተፈረሙትን ሥምምነቶች አተገባበርም በተመለከተ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ አምባሳደር ዲና ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ከሳውዲ አረቢያ ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የ2 ሚሊዮን ብር ጊዜያዊ እርዳታ ለማድረግ ወሰነች፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያረክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጰያ ሊቀ ጳጳስ በቀጣይም ቤተ ክርስትያኗ እርዳታውን አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራትና ጨምሮ በመንበራ ፓትርያርክ አዳራሽ ዛሬ በተደረገው አስቿኳይ ጥሪ ቤተክርስትያኗ ቀደም ሲል በገባችው ቃል መሠረት ለጊዜው የሁለት ሚሊዮን ብር እርዳታ አድርጋለች፡፡
ገንዘቡም በመጪው ማክሰኞ ለሚመለከተው አካል ገቢ ይደረጋል፡፡ ፓትርያርኩ እንደገለፁት ይህ የወገኖቻችን እርዳታ ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠው ወቅታዊ አጀንዳ መሆኑን በመግለፅ እስካሁን በመንግሥት በኩል እየተደረገ ያለውን የተቀናጀ አቀባበል በአካል በመጎብኘታቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡ ከሃይማኖት መሪዎች የሚጠበቀው በመንፈሳዊ አስተምህሮ ማፅናናትና መርዳት ባሻገር ወደ ቀድሞ ህይወታቸው እስኪመለሱ ድረስ መደገፍና መርዳት አስፈላጊ ነው ብለዋል ፡፡ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው ለወደፊቱም ከቅዱስ ፓትርያርኩ በሚሰጣቸው መመሪያ መሠረት ተመሳሳይ እርዳታ ለማድረግና አባታዊ ምክር ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ መንግሥት ብቻውን የስደተኞች ወገኖቻችንን ምግብና መጠለያ መሸፈን አይችልም ያሉት ተሰብሳቢዎቹ ለወደፊቱ በተቀናጀ መልክ እርዳታ በማሳበሳብ የወገኖቻችንን ህይወት እንዲስተካከል ጠንክረው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል፡፡
Sources : ENA and ERTA
tweet