10-12-2016![]()
(ዘ-ሐበሻ) በደርግ ዘመን ለአንድ ወር ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስተር ነበሩ:: ከዚያም በፊት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርነት አገልግለዋል:: ለረዥም ጊዜያት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርም የነበሩ ሲሆን በፋይናንስ ሚኒስተርነትም ኢትዮጵያን አገልግለዋል:: አቶ ተስፋዬ ዲንቃ (B.Sc. M.Sc, M.Ba)::
እኚህ ታላቅ ሰው ዛሬ ማረፋቸው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ:: የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ተስፋዬ ዲንቃ የተወለዱት አምቦ ሲሆን ሊባኖስ በሚገኘው አሜሪካን ስኩል ኦፍ ቤይሩት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን መቀበላቸውን የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል:: እንዲሁም ኒውዮርክ ከሚገኘው ሲራከስ ዩኒቨርስቲ በኢንጂነሪንግ ማስተርሳቸውን ሠርተዋል።
አቶ ተስፋዬ ዲንቃ ታሪክ ሲዘክራቸው የሚኖርበት ትልቅ ገድል አላቸው:: በተለይም በርካቶች የሚያስታውሷቸው ኢትዮጵያን ለሻአቢያ እና ለትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ያስረከበችው አሜሪካን የሞገቱበት ሙግት አይረሳም።
ተስፋዬ ዲንቃ ያረፉት በ77 ዓመታቸው ነው::
አቶ ተስፋዬ ባለትዳር፣ የ4 ልጀች